ወደ ክፍያ ገጽ ለመሄድ ይሄንን ይጫኑ / Click here to go to the payment page

Ethio Edir  ኢትዮ እድር

“WISH FOR THE BEST; PREPARE FOR THE WORST”




መተዳደሪያ ደንብ / Bylaws

 የኢትዮ እድር መተዳደሪያ ደንብ
 
ምዕራፍ 1 ጠቅላላ ድንጋጌ
 
አንቀጽ 1.1 ስያሜ

 1.1.1 ይህ እድር ኢትዮ እድር ተብሎ ይጠራል።

አንቀጽ 1.2 አድራሻና አቋም 

1.2.1 የእድሩ አድራሻ በዋሽንግተን ስቴት በስያትል ከተማ ነው።

1.2.2 እድሩ በዋሽንግተን ስቴት ሕግ መሰረት የተቋቋመና የሚሰራ ለትርፍ የማይሰራ ድርጅት ነው።

1.2.3 እድሩ የተቋቋመው ላልተወሰነ ጊዜ ነው።

አንቀጽ 1.3 ዓላማ

 1.3.1.3.1 የእድር አባል ወይም የአባል ቤተሰብ በሞት ሲለይ ለቀብር ስነ - ስርዓት ማስፈጸሚያ ወይም ለአስከሬን መላኪያ የሚሆን የገንዘብ እርዳታ ለማድረግ፣

1.3.2 አባል ወይም የአባል ቤተሰብ ሲሞት የእድሩ አባላት ለቅሶ እንዲደርሱና እንዲያስተዛዝኑ፣ ኢንፎርሜሽን ማዳረስና ማስተባበር፣

1.3.3 የለቅሶ ሥራን ማከፋፈል፣

1.3.4 አባላት የሟችን ቤተሰብ እንዲይጽናኑና በሚይስፈልገው ነገር ሁሉ እዲተባበሩ መንገር፣

1.3.5 ለቀብር አፈጻጸም ወይም ለአስከሬን ማጓጓዝ የሚያስፈልጉ መረጃዎችን ለሟች ቤተሰብ መስጠት፣

1.3.6 ለወደፊት ለአባላት ጥቅም ያስገኛል ብሎ የሚያምንበትን ማንኛውንም ዓላማ እንዳስፈላጊነቱ መጨመር

 

 አንቀጽ 1.4 ትርጓሜ

 1.4.1 በወንድ ጾታ የተገለጸው ለሴትም ያገለግላል።

1.4.2 እድር ማለት የኢትዮ እድር ማለት ነው።

1.4.3 አባል ማለት የኢትዮ እድር መተዳደሪያን ደንብ ተቀብሎ የተመዘገበ እና የአባልነት ግዳጁን የፈጸመ ያለ አባል ማለት ነው።

1.4.4 ቤተሰብ ማለት አባል፣የአባል ባለቤት፣ በእድሩ አባል ስር የሚተዳደርሩ እድሜያቸው 21 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ማለት ነው።

1.4.5 የነርሱና እነርሱ የሚለው እፃጻፍ፤ እርሷ፣እርሱ፣ የእርሱ፣ የእርሷ፣ የእነርሱ፤ የሚሉቱን ቃላቶች ሊተኩ ይችላሉ፡፡

 

አንቀጽ 1.5 የእድር ገቢ

1.5.1  ከአባልነት ክፍያ፣ - አንድ አባል እዲሁም አባል ከነቤተሰቡ (ባልና ሚስት፡ 21 ዓመት በታች ዕድሜ ካላቻው ልጆቻቸው ጋር) በዓመት $360 ዶላር ከሚከፈል፤
 1.5.2 
በስጦታ ከሚገኝ፤
 1.5.3
እድሩ የሚያዘጋጀውን ፕሮግራም ስፓንሰር ከሚያደርጉ ወይም እርዳታ ከሚሰጡ ድርጅቶች የሚገኝ ገቢ ይሆናል።

ምዕራፍ 2
 
አባልነት
 
አንቀጽ 2.1  አባል ስለመሆን

 
2.1.1 
በዋሽንግተን እስቴት የሚኖር ዕድሜው 18 እና ከዚያ በላይ የሆነ፣
 2.1.2 
የእድሩን ደንብና ሕግ የተቀበለ ማንኛውም ሰው አባል መሆን ይችላል።
 2.1.3 
አባል ከአካባቢው ለቆ በሌላ ቦታ መኖር ከጀመረ ግዴታውን በማክበር በአባልነት መቀጠል ይችላል።

 
አንቅጽ 2.2  የአባል መብት፣

2.2.1 አንድ አባል ከተመዘገበ ቀን ጀምሮ የመምረጥ መብት አለው።

2.2.2 አንድ አባል በአባልነት አንድ ዓመት ከሆነው የመመረጥ መብት ይኖረዋል።

2.2.3 አንድ አባል በአባልነት ሙሉ ዓመት ካልሞላው (ጎደሎ ዓምት/ fraction of a year) የገንዘብ ጥቅም አያገኝም። እድሩ ግን እራት ያበላል፡፡

2.2.4 አንድ አባል ከተመዘገበ ቀን ጀምሮ በቤተሰቡ ላይ በአስራሁልት ወራት ውስጥ ሞት የደረሰበት ከሆነ፣ እድሩ በሁለተኛው ቀን ለማስተዛዘን እራት ያበላል፣ ለሶስት (3) ቀናት ያስተናግዳል፣ ያስተዛዝናል። ይህ የሚሆነው በሲያትል (ፕጆት ሳውንድ / Puget Sound) አካባቢ ብቻ ነው፡፡ እራቱ በኢትዮጵያ ባሕል የተሠራ የአትክልት ምግብ (ጎመን፡ ሰላጣ፡ ክክ ቀይና አልጫ፡ እዲሁም ውሃ፡ ቦታው ከፈቀድ፡ እንደቡፌ ይቀርባል፡፡ ሰንጠረዥ 1 ይመልከቱ

2.2.5 ለማስተዛዘንና እራት ለማቅረብ ያልታሰበ ምክኒያት ከተፈጠረ፣ እድሩ ከሟች ቤተሰብ ጋር በመተባበር/ተመካክሮ እራቱን በአመቺ ጊዜ ያቀርባል፡፡ ይህ ድርጊት ሐይማኖትዊ ስነሥርእትን አያጠቃልልም። ለምሳሌ ያህል የእንድ አባል ቀብር ሌላ ቦታ ከነበር፣ቤተሰቦቹ ሲያትል ለለቅሶ ከተቀመጡ፣ እድሩ እራት ለማብላት ይተባበራል፡፡ነገር ግን የሐይማኖታዊ ስንሥራት (የወሩ፡ ያመቱ፡ ወዘተ) እድሩ አይተባበርም፡፡

2.2.6 አንድ አባል የአባልነት ግዴታውን ከአንድ ዓመት በላይ እያሟላ ከቆየ በኃላ፤ በአባሉ ወይም በባለቤቱ ላይ የሞት አደጋ ሲገጥም፤ አሥር ሺህ ዶላር ($10,000.00) ያገኛል። ሰንጠረዥ 1 ይመልከቱ

2.2.7 አንድ አባል የአባልነት ግዴታውን ከሁለት ዓመት በላይ እያሟላ ከቆየ በኃላ፤ በአባሉ ወይም በባለቤቱ ላይ የሞት አደጋ ሲገጥም፤ አሥራአምስት ሺህ ዶላር ($15,000.00) ያገኛል። ሰንጠረዥ 1 ይመልከቱ


2.2.8 አንድ አባል የአባልነት ግዴታውን ከሶስት ዓመት በላይ እያሟላ ከቆየ በኃላ፤ በአባሉ ወይም በባለቤቱ ላይ የሞት አደጋ ሲገጥም፤ ሐያ ሺህ ($20,000.00) ዶላር ያገኛል። ሰንጠረዥ 1 ይመልከቱ 2.2.9 21 ዓመት በታች የሆነ የአባል ልጅ የሞተ እንደሆነ አባል ከሚያገኘው 50% ያገኛል። ሰንጠረዥ 2 ይመልከቱ

2.2.10 የአባል ልጅ ሐያአንድ ዓመት (21) ሲሞላው፤ምንም ሳይዘገይ ወዲያውኑ የዓመቱን ክፍያ በመክፈል እራሱን ችሎ አባል ሊሆን ይችላል፡፡ የገባበት ዓመት ከጃንዋሪ አንድ (January 1 st) ጀምሮ እደገባ ይቆጠራል፡፡

2.2.11 እንደሙሉ አባል የተመዘገበበት ዓመት ላይ፡ ከወላጆቹ ጋር ሳለ የሚያገኘውን ጥቅም ያገኛል (አንቀፅ 2.2.9) ይመልከቱ፡፡ ዓመቱ ሲያልቅ፡ ሌላው አባል የሚያገኝውን ጥቅም ያግኛል፡፡ ሰንጠረዥ 2 ይመልከቱ

2.2.12.  ከአንድ በላይ በቤተሰብ ላይ ሞት ቢደርስ፣ የእድሩ ቦርድ አባላትንና ማሕበረሰቡን የገንዘብ እርዳታ እንዲያደርጉ ይጠይቃል፡፡

2.2.13.  ከዋሽንግተን እስቴት ውጭ አባል ከሞተ፤ ጉዳዩ እስከሚጣራ፣ እድሩ የተጠቃሚ ገንዘብ ክፍያን ያዘገያል፡፡ የሞት ምስክር ወይም ሌላ ሕጋዊ ወረቀት ማረጋገጫ ለመመልከት እድሩ የመጠየቅ መብት አለው፡፡

 ማሳሰቢያ፡ 

- አንድ አባል ከጠፋ ወይም የት እንደደረሰ የማይታወቅ ከሆነ፣ አባሉ የተጠቃሚ ክፍያ አያገኝም ፡፡

 - ከጥቅም ክፍያ ላይ፡ ያልተከፈሉ ወዝፍ እዳወች አስቀደመው ይቀነሳሉ፡፡

  - ኤሌክትሮኒክ ክፍያ እስከሚጀመር፣ ክፍያ ሁሉ በቸክ ወይም በመኒ ኦርደር (check/money order) ነው፡፡

  - ልሕክምና ወይም ለሌላ ምክኒያት፡ እድሩ ቅድመ ክፍያ አያደርግም፡

አንቀጽ 2.3 የአባል ግዴታና የባልና ሚስት መብት  

 
2.3.1 
የእድሩ ደንብ የሚጠይቀውን መፈጸም፤
 2.3.2 
የአባልነትና ሌሎች ቅጾችንም በአግባቡ በትክክል ሞልቶ ለእድሩ የመስጠት፤
 2.3.3
መደበኛ የአባልነት መመዝገቢያና ሌላም በሞት ጊዜ ለሚደረጉ መዋጮዎች በወቅቱ መክፈል፤።
 2.3.4 
አስገዳጅ ሁኔታ ካላጋጠም በስተቀር በጠቅላላ ስበሰባ ላይ መገኘት፤
 2.3.5
በአባላት መካከል የመግባባትና የመተባበር ስሜት አንዲዳብር መርዳት፤
  2.3.6
አባል ወይም የአባል ቤተሰብ በሞት ከተለየ እያንዳንዱ የእድሩ አባል ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ካላጋጠመ በስተቀር፣ለቅሶ መድረስና እዚህ የሚቀበር ከሆነ በቀብሩ ላይ መገኘት፣ አስክሬኑ ወደ አገር ቤት ወይም ሌላ ቦታ የሚሄድ ከሆነም መሸኘት፤

 2.3.7  አባል ወይም የአባል ቤተሰብ በሞት ከተለየ፣ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቅ አባል ለእድሩ ተጠሪ ማሳወቅ፤
  
2.3.8  የአባል ወይም የአባል ቤተሰብ ሁኔታ ከተለወጠ፣ (ለምሳሌ የልጅ እድሜ 21 በላይ ከሆነ፣ ወይም ባልና ሚስት ከተፋቱ፣) ለውጥ ከሆነበት ቀን ጀምሮ 30 ቀናት ውሰጥ ለውጡን ለእድሩ ማሳወቅ ይኖርበታል።

 2.3.9  በተጨማሪም በቤተሰብ ውስጥ ተጨማሪ አዲስ ልጅ ከተወለደ ወይም 21 ዓመት በታች የሆነ የአባል ልጅ ከኢትዮጵያ ወይም ከሌላ ሥፍራ በማምጣት ቤተሰቡን ከተቀላቀለ ለያንዳንዱ ተጨማሪ ልጅ የመመዝገቢያ መቶ ዶላር ($100.00) በመክፈል አባል ይሆናሉ። ማሳሰቢያ ከላይ የተጠቀሰው አባል ከነልጆች የተመዘገበን አይመለከትም

2.3.10 ባልና ሚስት በአንድ ቀን ከተመዘገቡ፤ የአባልነት መብታቸው እኩል ነው፡፡ በምዝገባ ላይ ሁለቱም መገኘት አለባቸው፡፡
 2.3.11
አባልና የአባል ባለቤት በተለይየ ጌዜ ከተመዘገቡ፤ የእያንዳዳቸው መበት የሚጀምረው ከተመዘገቡበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡ 
 2.3.12
አባልና የአባል ባለቤት በሕጋዊ መንገድ ከተፋቱ፤ ኢትዮ እድር ማንኛውንም የአባልነት ባለቤትነት ሕጋዊ ውሳኔ ያከብራል፡፡ ሕጋዊ ውሳኔ፣ የባልና የሚስት የግል ስምምንትን በኖተራይዘድ (notarized) ደብዳቤን ያጠቃልላል፡፡ 2.3.8 ይመልከቱ፡፡ አባል ሁኖ የቀረው፡ የውዝፍ እዳውን ኃላፊነት ይወስዳል፡፡
2.3.13
የተፈታው አባል የዓመቱን መዋጮ ብቻ በመክፈል እንደአባል ወዲያውኑ (በተፋቱበት ቀን) ሊቀጥል ይችላል። ካልቀጠለ ግን፡ የሞት አደጋ ቢያጋጥም፤ የተጠቃሚ ክፍያውን ያጣል፡፡

አንቀጽ 2.4 የአባልነት መመዝገቢያና ዓመታዊ ከፍያ  

 
2.4.1 

የአባነልነት መዝገቢያ

አንድ ጊዜ ብቻ

ዓመታዊ

- ግለሰብ                                                   

$100.00               

+      $360.00

- አባልና ባለቤት                                         

$200.00               

+       $360.00

-ያላገባ ከልጅ ጋር                                      

$150.00               

+       $360.00

-አባልና ባለቤት ከልጆች ጋር       (አንቀፅ 2.3.9 ልከቱም) 

- የቤተሰብ ለውጥ (ባለቤት ወይም ልጆች) እያዳዳቸው (per person)   መመዝገቢያ

              

$250.00  



 $100.00          

+       $360.00



2.4.2 
አባል እዲሁም አባል ከነቤተሰቡ (ባል፣ሚስትና ዕድሜአቸው 21 ዓመት በታች የሆኑ ልጆችን ጨምሮ) በየወሩ $30 ዶላር ታስቦ በዓመት ሁለት ጊዜ፡ $180.00 (አንድ መቶ ሰማኒያ) ዶላር፣ ወይም በጠቅላላው በዓመት $360.00 (ሶስት መቶ ስልሳ) ዶላር አንድ ጊዜ ይከፍላሉ።
 2.4.3
በወረረሽኝ በሽታ ወይም በከፍተኛ አደጋ ምክኒያት፡ የተጠቃሚ ክፍያው እድሩ ካለው ገንዘብ በላይ ከሆነ፣ ጠቅላላ ስብሰባ ተጠርቶ፡ ወይም የእድሩ ቦርድ አባላት በወሰኑት የተጠቃሚ ክፍያ ማስተካከል ይደረጋል፡፡ 
 2.4.4 
የእድሩ ተቀማጭ ገንዘብ ከመቶ ዶላር ($100,000) በታች ከሆነ፤ አባላት ተጨማሪ መዋጮ እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ። በዚህ ጊዜ ባልና ሚስት እያንዳዳቸው ተጨማሪ መዋጮውን እደሌላው አባል እኩል ያዋጣሉ፡፡ መዋጮው በአባላቱ በስብሰባ ላይ ይወሰናል፡፡

ምዕ 3

 አንቀጽ 3.1 የሥነ ሥርዓት እርምጃ


 3.1.1
የአባልነት ክፍያ የሚሰበሰበው ዓመቱ ሲጀመር ነው፡፡ አንድ አባል ክፍያውን አላሟላም የሚባለው በዓመት መክፈል የሚገባውን ክፍያ ሳይከፍል የመክፈያው ዓመት ካለፈ ነው፡፡ ካለፈ ግን የመቶ ብር ($100) ይቀጣል፡፡ የአባልነት ክፍያውን ላላሟላ አባል፡ የስልክ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል። አንቀፅ 2.3.3. ይመልከቱ፡፡


 3.1.2 
አንድ አባል መክፈል የሚገባውን ክፍያ ሳይከፍል የመክፈያው ዓመት በስድስት (6 month) ወር ካለፈ: በገዛ ፈቃዱ እንደለቀቀ ተቆጥሮ ከአባልነት ይሰናበታል፡፡ የገንዘብ ወይም የእራት ጥቅሙም ይሰረዛል፡፡

1.    


3.1.3
አንድ አባል ለረጅም ጊዜ ከአገር (USA) ውጭ የሚቆይ ከሆነ፡ ቅድመ ክፍያ ለዓመታት ሊያደርግ ይችላል፡፡
3.1.4
የአባልነት ግዴታውን ባለመክፈሉ የተሰናበተ አባል እንደ አዲስ ሊመዘገብ ይችላል። የአባልነት መብቱም እንደ ማንኛውም አዲስ አባል ይሆናል።

3.1.5  አንድ አባል የሐሰት መረጃ ለእድሩ ከሰጠና በዚህም የሃሰት መረጃ ምክንያት ሊሰጠው የማይገባውን ገንዘብም ይሁን ሌላ ጥቅም ለማግኘት ጥረት ሲያደርግ ከተገኘ እና ከተረጋገጠ፣ እድሩ አባልነቱን ሊሰርዝ ይችላል። ያገኘውም ጥቅም ካለ፣ እንዲመልስ እድሩ በህግ ይጠይቀዋል።

 3.1.6  አንድ የእድር አባል ከአባልነት ከተገለለ፣ አባል በነበረበት ወቅት ለዕድሩ የከፈለው ማንኛውም ገንዘብ  አይመለስለትም።
 3.1.7
የተገለለውን አባል፣ እድሩ ሁለተኛ ለአባልነት አይቀበለውም፡፡  

አንቀጽ 4  
የእድሩ የአመራር አካላት
 

ዕድሩ ጠቅላላ ጉባኤ፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ፣ የሥራ አስፍጻሚ፣ባለ አደራ ቦርድና ኦዲተር ይኖረዋል።

አንቀጽ 4.1

 ጠቅላላ ጉባኤ

 
4.1.1
ጠቅላላ ጉባኤ ማለት የእድሩ አባላት የሚገኙበት ጠቅላላ ስብሰባና የዕድሩ ከፍተኛ የሥልጣን አካል ነው።
4.1.2
ጠቅላላ ጉባኤው በዓመት ሁለት ጊዜ ይጠራል። ሁለትኛው ለሽርሽር (picnic) ነው።
4.1.3
ከግማሽ በላይ አባላት የተገኙበት ጠቅላላ ስብሰባ ምልዓተ ጉባኤ ይሆናል።
4.1.4 
ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ ምልዓተ ጉባኤ ካልሞላ፣ ተከታይ ሁለተኛ ስብሰባ ጠርቶ የሚገኙ አባላት ከግማሽ በታች ቢሆኑም። ስብሰባው እንደምልዓት ጉባኤ እንደሞላ ይቆጠራል።
4.1.5
ከላይ በአነቀጽ 4.1.3 እና 4.1.4 በተጠቀሰው መሰረት ምልዓተ ጉባኤው በታች በአንቀጽ 4.1.6 የተጠቀሰውን ሳያጨምር ሌላ ማንኛውንም ውሳኔ ማስተላለፍ ይችላል።
4.1.6 
እድሩን ለማፍረስ የጠቅላላ ጉባኤው ሁለት ሶስተኛው (2/3) ድምጽ ያስፈልጋል።
4.1.7 
እድሩ የፈረሰ እንደሆነ፣ የእድሩ ተንቀሳቃሽና የማይነቀሳቀስ ንብረት፣ ጥሬ ገንዘብ ጭምር በስያትል ለሚገኘው የኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ (Ethiopian Community in Seattle) እንዲሰጥ ይደረጋል።

አንቀጽ 4.2 የጠቅላላ ጉባኤ ተግባርና ሥልጣን


4.2.1 
የዳይሬክተሮች ቦርድ ይመርጣል፣
4.2.2 
የእድሩን መተዳደሪያ ደንብ ያጸድቃል፣ ያሻሽላል፣
4.2.3
የእድሩን የሥራ ማስኬጃ ወጭ ይፈቅዳል፣
4.2.4 
ኦዲተሮችን ይመርጣል፣
4.2.5
የእድሩን ገቢ አሰባሰብ፣ ወጪ አደራረግና ሌሎች የእድሩን የገንዘብ አጠቃቀምና እንቅስቃሴ በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣
4.2.6 
የቦርዱን ሪፖርት ያዳምጣል፣ ይመረምራል፣ እንደአስፈላጊነቱም መመሪያዎችን ይሰጣል።

አንቀጽ 4.3

የዳሬክተሮች ቦርድ


የእድሩን ስራ በቅርብ እንዲቆጣጠር በጠቅላላው ጉባኤ የሚሰየም አንድ የዳሬክተሮች ቦርድ ይሰየማል፡፡

                                                         ተግባራቱም የሚከተሉት ይሆናል፡፡ 
 

4.3.1
የቦርድ አባላት ቁጥር ዘጠኝ ይሆናል፡፡
4.3.2
የቦርዱ አባላት የሥራ ዘመን ሁለት ዓመት ይሆናል። ነገር ግን ባልተጠበቀ ምክኒያት የአባላቱ የሥራ ዘመን ለሁለት የሥራ ዘመን ሊራዘም ይችላል፡፡ 
4.3.3
በሁለት የሥራ ዘመናት በተከታታይ ያገለገለ የቦርድ አባል በድጋሚ ለመመረጥ ቢያንስ ለአንድ ዓመት በቦርድ አማካሪነት ማገልገል ይኖርበታል። በቦርድ ስብሰባ ውሳኔ ላይ አይመርጥም፡፡
4.3.4
የቦርዱ አባላት ከግማሽ በላይ ከተገኙ ምልዐተ ጉባኤ ይሆናል።
4.3.5 
በማናቸውም የቦርድ ምርጫ ጊዜ ከአባላቱ ከሚቀርቡት ውስጥ የስራ ዘመናቸውን የጨረሱ የቦርድ አባላት ቁጥር 50 በመቶ ወይም ከግማሽ ሊበልጥ አይችልም።
4.3.6 
አንድ የቦርዱ አባል የሥራ ዘመኑን ሳይጨርስ አገልግሎቱን በማናቸውም ምክንያት ቢያቋርጥ ለቀሪው የሥራ ዘመን ተክቶ የሚያገለግል አባል ቦርዱ ከአባላት መሃል ይሰይማል።
4.3.7 
በማናቸውም የቦርድ አባላት ምርጫ ጊዜ የቦርዱ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሆነ አባል ተመልሶ ለቦርድ አባልነት ቢመረጥ ቀድሞ ይዞት የነበረውን የስራ አስፈጻሚ ስፍራ መልሶ ሊይዝ አይችልም።

አንቀጽ 4.4  

የዳይሬክተሮች ቦርድ ተግባርና ስልጣን የሚከተሉት ይሆናል።

 
4.4.1 
ከቦርዱ አባላት መካከል ቦርዱ ሰባት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን ይመርጣል።
4.4.2 
የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የእድሩን ስራ ለማካሄድ የሚያወጣቸው የአፈጻጸም ስርዓቶችን ይመረምራል፣ ያጸድቃልም።
4.4.3 
የሥራ አፈጻጸም ዘገባ ለጠቅላላ ጉባኤ በተወሰነ ጊዜ ያቀርባል።
4.4.4
የእድሩ ወጪ በጠቅላላ ጉባኤ ከተፈቀደው በላይ አለመሆኑን ይቆጣጠራል፣ ወጪው ከተፈቀደው መጠን ከአስር በመቶ (10%) በላይ ከሆነ ይህ የሆነበትን ምክንያት ለጠቅላል ጉባኤው ያስረዳል።
4.4.5 
ማንኛውም የቦርዱ አባል ለእድሩ ለሚሰጠው አገልግሎት ክፍያ ወይም መደጎሚያ አይደረግለትም።

4.4.6  እንደ አስፈላጊነቱ የእድሩ ሊቀመንበር በእድር ጉዳይ ላይ ልምድ ወይም እውቀት ያላቸውን የእድሜ ባለጸጋ ኢትዮጵያውያንን ወይም ከሌላ አገር ይጋብዛል። ሆኖም ግን እነዚህ አማካሪዎች ልምዳቸውን ከማካፈልና ሃሳብ ከመስጠት ውጭ በቦርድ ስብሰባ ላይ ድምጽ አይሰጡም።
4.4.7
የቦርድ ምርጫ በሁለተኛው ዓመት በሚደረግ ስብሰባ ይሆናል፡፡

 አንቀጽ 4.5  የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴና ኃላፊነት 

 
የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ፣አንድ ሊቀመንበር፣ አንድ ምክትል ሊቀመንበር፣ አንድ ፀሃፊ፣ አንድ አቃቤ ንዋይ ( ገንዘብ ያዥ)

እንድ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ፣  አንድ የኦፕሬሽንና የቴክኖሎጂ ኃላፊና፣ አንድ የሂሳብ ባለሙያ (አካውንታንት) ያሉበት ባለ ሰባት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያቋቁማል፡፡ ይህ ኮሚቴም የሚከተሉት ተግባራት ያከናውናል።

4.5.1 የእድሩን የእለተ ከእለት ተግባር የሚያከናውን አንድ ሊቀመንበር፣ አንድ ምክትል ሊቀመንበር፣ አንድ ፀሃፊ፣ አንድ አቃቤ ንዋይ (ገንዘብ ያዥ)፣ይመርጣል፡፡
 4.5.2 
ለሥራው ክንውን የሚረዱ የስራ አፈጻጸም ስርዓቶች ያሰናዳል። በቦርድ ሲጸድቅም በሥራ ላይ ያውላል።
 4.5.3 
የዕድሩን ሥራ ለማከናወን አስፈላጊ የሆኑ ንዑሳን ኮሚቴዎች ያቋቁማል፣ መመሪያ ያወጣል፣ መደበኛ ስራውን ያከናውናል።
 4.5.4 
እንደ አስፈላጊነቱ በየጊዜው እየተገናኘ መደበኛ ስራውን ያከናውናል።
 4.5.5 
ለቦርዱ የሥራ ክንውን ዘገባ በተወሰነ ጊዜ ያቀርባል።
 4.5.6 
የእድሩን ገቢ ያሰባስባል።
 4.5.7
ቅጾችን አዘጋጅቶ ሥራ ላይ ያውላል።
 4.5.8
በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት እርዳታ ይሰጣል።
 4.5.9 
አስፈላጊ ኢንፎርሜሽን ለአባላት በወቅቱ አንዲደርስ ያደርጋል።
 4.5.10 
የእድሩን ገንዘብና ንብረት በአግባቡ ይይዛል።

 4.5.11  የእድሩ አሠራር የሚሻሻልበት መንገድ እያጠና በቦርድ ሲፈቀድ ስራ ላይ ያውላል።

አንቀጽ 4.6

 ሊቀመንበር


4.6.1
የቦርዱን የሥራ አስፈጻሚውን ኮሚቴ ስብሰባ በሊቀ-መንበርነት ይመራል።
 4.6.2
የእድሩ ስራ በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት አንዲከናወን ያቅዳል፣ የእድሩን ስራ ይመራል፣ አባላትን ያስተባብራል፣ይቆጣጠራል።
 4.6.3
የእድሩ ሥራን ይመራል ፡፡ በየጊዜው ለሚደረገው የዳይሬክተሮች ቦርድ ስብሰባን ያስተባብራል፡፡
 4.6.4 
የሥራ ክንውን ዘገባ በየጌዜው ለሚሰበሰበው ለዳይሬክተሮች ቦርድ ያቀርባል።
  4.6.5
የዳይሬክተሮች ቦርድን ስብሰባ ይጠራል፡፡ አስቸኳይ ሁናቴ ካጋጠመው ጠቅላላ ጉባኤ እንዲሰበሰብ ሃሳብ ያቀርባል።
 4.6.6
የወጭ ማዘዣዎችንና ደብዳቤዎችን በዕድሩ ስም ይፈርማል።

እንቀጽ 4.7

 ምክትል ሊቀመንበር

 
4.7.1
ሊቀመንበሩ በማይገኝበት ጊዜ ሊቀመንበሩን ተክቶ የእድሩን ሥራ ያከናውናል።


 
አነቀጽ 4.8   ጸሐፊ


 4.8.1
የዕድሩን አባላት የስም ዝርዝር ይይዛል።
 4.8.2
የቦርዱንና የስራ አስፈጻሚውን ኮሚቴ አጀንዳ አዘጋጅቶ ሊቀመንበሩ ሲፈቅድ በየወሩ የስራ አስፈጻሚው ኮሚቴ አባሎችን፣ በየሶስት ወሩ የባለአደራ ቦርድ እባላትን እንዲሁም በየጊዜው ሲወሰን የእድሩን ሙሉ አባላት ለስብሰባ ይጠራል።
4.8.3
የስብሰባዎችን ቃለጉባኤ ይይዛል፣ ያዘጋጃል፣ ለቦርዱ ያቀርባል።
4.8.4
የእድሩን ጽህፈት ቤት ሥራ ያከናውናል። በተጨማሪም መዝገብ፣ ያለቁ የደረሰኝ ግልባጮች፣የመንግሥት ደብዳቤወች፡ የፍቃድ ወርቀቶች፣ወዘት ይይዛል። የቦርድ አባላት ወይም ጉባየው ሳያውቅ፡ አንድም የእድሩ ወረቀት አይቃጠልም ወይም አይጥልም። 

አንቀጽ 4.9 ገንዘብ ያዥ

 
4.9.1
በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት ለእድሩ ገቢ ሊሆን የሚገባውን ገንዘብ በየጊዜው እየሰበሰበ በእድሩ የባንክ ሂሳብ ያስቀምጣል።
4.9.2
በመመሪያው መሰረት ዕድሩ ለአባሎች የሚሰጠውን ዕርዳታ ወይም ክፍያ ቦርዱ ሲወስን ይፈጽማል።
4.9.3
ቼኮች በሁለት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባሎች መፈረማቸውን ያረጋግጣል፡፡
4.9.4
የእድሩን ሥራ ማካሄጃ በጀት ያዘጋጃል፣ ሲጸድቅም በሥራ ላይ ያውላል።
4.9.5
ወጪዎቹ በበጀት ከተፈቀደው በላይ አለመሆናቸውን ይከታተላል።

አንቀጽ 4.10 የሂሳብ ሹም (አካውንታንት)

 
4.10.1
የእድሩን የሂሳብ መዛግብት ይይዛል።
4.10.2
የእድሩን የገቢና የወጪ ደረሰኞች ይይዛል።
4.10.3
ገቢዎች በአግባቡ የተሰበሰቡ መሆኑን መርምሮ ያረጋግጣል።
4.10.4
የባንክ ደብተሮች ይይዛል፣ ያስታርቃል።
4.10.5
የእድሩን ሂሳብ ሪፖርት ያዘጋጃል፣ ያቀርባል።
4.10.6 
በመንግስት ተቋማት የሚጠየቅ የሂሳብና የታክስ ሪፖርት ያዘጋጃል።

አንቀጽ 4.11 የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ


 4.11.1
በማንኛውም እድሩን በሚመለከት ሁኔታ የሚደረገውን የማሰተዋወቅ ሥራ ያከናውናል።
4.11.2
ከተለያዩ ተመሳሳይ ዓላማ ያላቸው ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ይመሰርታል።
4.11.3
እድሩን ለማስተዋወቅና ለማሳደግ የሚረዱ ጽሁፎችን አያዘጋጀ በየቦታው ይበትናል።
4.11.4 
ማንኛውንም የዕድሩን ጉዳይ በተመለከተ አስፈላጊውን መረጃ ለአባላት ያስተላልፋል ወይም መተላለፍን ያረጋግጣል።
4.11.5
የእድሩን ዓላማ ሊያግዝ ከሚችሉ ተቋማት ሊገኝ የሚችለውን ጥቅምና እርዳታ እየተከታተል ለቦርዱ ያቀርባል።
4.11.6
የእድሩን ዓላማ ለማስፈጸም ከሚያግዙ ተቋማት ጋር ግንኙነት በመመስረት ስለዝርዝር ሥራቸው ለቦርዱ ሪፖርት በማቅረብ ዕድሩ በተሻለ ሁኔታ አገልግሎች የሚያገኝበትን መንገድ ያበጃል።

አንቀጽ 4.12 የኦፕሬሽንና ቴክኖሎጂ ኃላፊ

4.12.1 የእድሩ አሠራር በሚቀላጠፍበት ሁኔታ ላይ አጠቃላይ ጥናቶችን እያደረገ ሪፖርቱ ያቀርባል።
4.12.2
ስለ ቀብር ቤቶች፣ትራንስፖርት፣ ፓሊስ፣ እና ሰለመሳሰሉት ከዕድሩ ሥራ ጋር ሰለሚገናኙ ተቋማትና አገልግሎቶች አስፈላጊውን ጥናት እና ክንውን ሪፖርት ለቦርዱ ያቀርባል።
4.12.3 
ዕድሩ ከጋራ ዋስትና ወይም መድሕን ተጠቃሚ የሚሆንበትን መንገድ አጥንቶ ለቦርዱ ሪፖርት ያቀርባል።
4.12.4
የእድሩን ዓላማ ለማስፈጸም ያግዛሉ ተብለው የሚገመቱ ኮሚቴዎችን የማቋቋም ጥረቱን በኃላፊነት ይመራል።
4.12.5
ዕድሩ ሕጋዊ አካል ለማግኘትና ይህን ይዞ ለመቆየት የሚያስፈልገውን ሁኔታ በመከታተል ስራ ላይ ያውላል።
4.12.6
የእድሩን ድህረ-ገጽ የማቋቋሙን፣ የማስተደደሩንና የማሳደጉን ጥረት በኃላፊነት ይመራል።
4.12.7
የዕድሩን የዶመይን (ድህረ ገጽ) ስም ያስመዘግባል፣ ምዝገባውም አንዳያልፍበት በየዓመቱ አስፈላጊውን ዕድሳት ያደርጋል።
4.12.8
አባላት የዕድሩን ድህረ ገጽ በሚገባ የሚጠቀሙበትን ሁኔታ እያጠና ለቦሩድ በማቅረብ ጥናቶችን ስራ ላይ ያውላል።

አንቀጽ 4.13 ኦዲተር


 4.13.1 
የዳሬይክተሮች ቦርድ ከጠቅላላ ጉባኤው ውስጥ ሶስት አባላት ያሉበት ኦዲተሮችን ይሰይማል።
4.13.2 
የኦዲተሮቹም ተጠሪነት ለጠቅላላ ጉባየ ይሆናል።
4.13.3 
ኦዲተሮቹም በሂሳብ ባለሙያው ተዘጋጅቶ የቀረበውን ዓመታዊ ሪፓርት መርምረው የደረሱበትን ለቦርዱ ያቀርባሉ።
4.13.4
ቦርዱ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ኦዲተሮቹ ሙሉውን ዓመት የሚያጠቃልል፣ የወራት፣ የሩብ ዓመት፣  ወይም የግማሽ ዓመታት ሪፖርቶችን እንዲያቀርቡ ሊጠይቅ ይችላል።

ምእራፍ 5 ባለ-አደራ ቦርድ
 
አንቀጽ 5.1 አመሠራረትና ኃላፊነት


 
5.1.1
አምስት (5) አባላት ያሉበት ባለ-አደራ ቦርድ ከጠቅላላው ጉባኤ አባላት ይሰየማሉ።
5.1.2
የእድሩ ምክትል ሊቀመንበርና የሂሳብ ሹም ምንጊዜም የባለ-አደራ ቦርድ አባል ይሆናሉ፡፡ የእድሩ አባላትሶስት (3) ሌላ ሰወች ይመርጣሉ፡፡
5.1.3
ከተመረጡት አንዱ የባለ-አደራ ቦረድ ሰብሳቢ ይሆናል፡፡
5.1.4
የባለ-አደራ ቦርድ በቀጥታ ተጠያቂነቱ ለኢትዮ እድር ጠቅላላ ጉባዔ ይሆናል። 
5.1.5
ለባለ-አደራ ቦርድ ከተመረጡት አንዱ ሥራዉን በሆነ ምክኒያት ሊቀጥል ባይችል፤ ሐላፊነቱን ቢያስረክብ፤ ወዲይውኑየማሕበሩ ዋና ቦርድ ሌላ ይተካል ለአባላትም ያስታውቃል።
 5.1.6
የባለ-አደራ ቦርድ ከኢትዮ እድር ዳሪክተሮች ቦርድ ጋርና፣ ከሌላው አባል ጋር በመነጋገርና በመመካከር፤ ኢትዮ እድር ላለው ገንዘብና ንብረት ጥበቃና ደህንነት ተባብሮ ይሠራል ይቆጣጠራልም።
5.1.7
ከአሥር ዶላር ($10,000.00) በላይ ወጭ ሲሆን (ከተጠቃሚ ክፍያ ሌላ) የባለ አደራ ቦርድ ማጽድቁን በጹሑፍ ይገልጣል።
5.1.8
የባለ-አደራ ቦርድ ጎድሎ አሠራርን ከተገነዘበ፤ መጀመሪይ ጉዳዩን ወደ እድር ቦርድ ይቀረባል፡፡ አጥጋቢ ውጤት ካላገኘ፤ ጉዳዩን ወደ ኢትዮ እድር ጠቅላላ ጉባዔ ያቀርባል፡፡ ሰቸኻይ ጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል፡፡
5.1.9
የአባላትን እሮሮ በቦርድ ላይ ያለዉን ይቀበላል። 
5.1.10 
ቢቻል በየወሩ ካልተቻለ በየሶስት ወሩ፣ ክባንክ ያለውን ገንዘብ እንዲሁም የእድሩን ንብረት ያገናዝባሉ፡፡

አንቀጽ 5.2 የባለ-አደራ ቦርድ ምርጫና የሥራ ዘመን


5.2.1
ለባለ-አደራ ቦርድ አባልነት የሚመረጡ ሶስቱ (5) እጩዎች ለሶስት (3) አመታት ያገለግላሉ።
5.2.2 
ከአባል በሥራ ስንብት ምክንያት ክፍት ቦታ ቢኖር፣የኢትዮ እድር ቦርድ እስከቀጣዩ ጠቀላላ ስብሰባ ድረስ ተተኪ ባለአደራ አባላን መሰየም ይቻላል።
5.2.3
የባለአደራ ቦርድ አባላት፣ የሥራ ዘመናቸው ሲያበቃ፣ በድጋሚ ተመርጠው ለማገልገል የሚያግዳቸው አይኖርም።

ምእራፍ 6  የእድሩ ሕገ-ደንብ (Bylaw) 

6.1  ይህ ሕገ-ደንብ 2020 የተሻሻለ የኢትዮ እድር ሕገ-ደንብ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል። January 1st, 2022 ጀምሮ በሥራ ላይ ይውላል።
6.2 
የኢትዮ እድር አመታዊ የስራ አፈፃፀም እና የሒሳብ አያያዝ January 1st የሚጀምር ሲሆን የዓመቱ ሒሳብ December 31st ይዘጋል። (Annual cycle will be January 1st to December 31st).

 


The Bylaws of Ethio Edir

Article 1. General Rules

Article 1.1. Designation

1.1.1.     The name of this self-help organization is called Ethio Edir.

Article 1. 2. The Address and Establishment

1.2.1.     The Edir is in the City of Seattle in Washington.

1.2.2.     The Edir is a nonprofit organization established according to the laws of the state of Washington.

1.2.3.     The Edir is established for an indefinite period.

 

Article 1.3. The Objective

1.3.1.     To provide financial assistance for funeral services and transporting the body of a member of the Edir to a final resting place.

1.3.2.     To disseminate information about a member's death to the members of the Edir.

1.3.3      To coordinate and assign the tasks associated with the death of a member.

1.3.4.     To encourage members to be present in mourning and console the deceased's surviving family members.

1.3.5.     To provide the necessary information about funeral services or for transporting the body of a deceased member to the family members.

1.3.6.     To add any other objective that is believed to be necessary for the usefulness of the members.

 

Article 1.4. Definition

1.4.1.     The following information applies to all genders equally.

1.4.2.     Edir means Ethio Edir.

1.4.3.     A member is registered upon accepting the Ethio Edir Bylaws and meeting the membership obligations.

1.4.4.     A family equates to a spouse and children under twenty-one registered as members of the Edir.

1.4.5      Their or they equate or apply to her, his, or them.

Article 1.5. The Income of the Edir

1.5.1.     Membership fee – from a single member or a member with their family (husband, wife, and children under 21) payment of three hundred sixty dollars ($360.00) per year.

1.5.2.     From Donors/supporters.

1.5.3.     Donations may be obtained from donors or organizations that sponsor the events organized by Edir.

 

Article 2. Membership

Article 2.1. Being a Member

2.1.1.     A person who lives in Washington State and is aged eighteen or over.

2.1.2.     Anyone who accepts the Bylaws and regulations of Ethio Edir can be a member.

2.1.3.     A member who leaves the area and lives in another area can continue their membership by fulfilling their obligations.

 

2.2. The Rights of the Member

2.2.1.     A member can vote from the date they are registered.

2.2.2.     A member has the right to be elected if they have been a member for a year.

2.2.3.     A member will not get a financial benefit for a fraction of a year. But the Edir will serve dinner.

2.2.4.     If death occurs among members, the Edir will serve the mourners an Ethiopian vegetarian dinner (Enjera, collard greens, salad, split pea/lentils red and yellow) and water on the second night of the mourning and console and support them for three (3) days. The food will be served in buffet style if the place allows it.

2.2.5      If the mourning gathering is impossible and the Edir cannot serve a meal due to unexpected circumstances, the dinner will be served appropriately after consultation with the deceased family at the right time. For example, if the funeral service was held outside of Washington state and the family planned a memorial gathering in Seattle, the Edir might serve dinner. This gathering should not have any influence on religion. Refer to Tables 1 and 2.

2.2.6.     If a member stays in their membership for one year, fulfilling the second (2) year membership obligations, and if death occurs, they will get ten thousand dollars ($10,000.00). Refer to Article 2.2.3 and Table 1.

2.2.7.     If a member stays in their membership for three (3) years fulfilling their membership obligations, and if death occurs, they will get fifteen thousand dollars ($15,000.00). Refer to Article 2.2.3 and Table 1.

2.2.8.     If a member stays in their membership for four (4) years or more, fulfilling their membership obligations, and if death occurs, they will get twenty thousand dollars ($20,000.00). Refer to Article 2.2.3 and Table 1.

2.2.9.     If a child of a member under twenty-one dies, the member (parent) will get 50% of the beneficiary benefit. Refer to Tables 1 and 2.

2.2.10    A member child registered within the family can become a full member immediately (not even a day late) after turning 21 years old by paying only the annual fee. Refer to Tables 1 and 2.

2.2.11    In the first year, the child, as a full member, will carry over the benefit he would have received staying with the parents (article 2.2.9). After that, the beneficiary payment becomes the same as all other members. Refer to Table 1

Child Benefit at Age 21 Transition

Benefit

0-12 Months

(if death occurs)

1st yr. (over 12 months)

2 yrs. +

3rd yr. +

4th year

5th year

Parent

Dinner

$10,000 + Dinner

$15,000 + Dinner

$20,000 + Dinner

$20,000 + Dinner

$20,000 + Dinner

Child, 50% of parent benefits

Dinner

$5, 0000 + Dinner

$7,500 + Dinner

$10,000 + Dinner

$10,000 + Dinner

$10,000 + Dinner

A Child @ 21 (determine at what year became 21)

Dinner +

$5000 or

$7500 or

$10,00

$10,000 + Dinner

$15,000 + Dinner

$20,000 + Dinner

$20,000 + Dinner

$20,000 + Dinner

Table 1

2.2.12    If more than one person dies in a member's family, the Board may request more donations from Ethio Edir members and the community.

2.2.13    If a member passes away outside of Washington state, the beneficiary benefit will not be released until the circumstances of the death are investigated. The Edir may request a death certificate or other legal documents.

 

Note:           - There is no beneficiary payment for a missing person/member.

- All unpaid balances will be deducted in advance from beneficiary payment.

- All payments should be in check/money order till electronic payment is available.

            - The Edir will not make any payment for medical or other reasons.

 

 

 

Article 2.3. The Obligation of the Member

2.3.1.     Fulfilling what the Bylaws of the Ethio Edir require.

2.3.2.     Correctly fill out the membership application and other pertinent forms of Edir and return them to Edir.

2.3.3.     Paying membership registration fees, annual dues, and contributions determined by the General Assembly on time.

2.3.4.     Unless unforeseen circumstances occur, members must attend the general meetings.

2.3.5.     Providing help to reach an agreement and cooperation among the members.

2.3.6.     When a member dies, unless there is an unforeseen circumstance, members of the Edir should be present at the mourning, burial, or farewell service of a member's body before being transported to the country of origin (to the final resting place). Members are not obliged to attend if the service is out of the organization's location.

2.3.7.     When a member passes away or has any life change, a member who knows the issue closely is responsible for informing the Edir.

2.3.8.     If there is any change in the member's status, such as when a child's age is over twenty-one, divorce, address, email, phone number, etc., the member should notify the Edir Board Members within 30 days.

2.3.9.     If a newborn in the family or a child whose age is below 21 joins the family legally from Ethiopia or another location, each new child can be a member by paying a one-time registration fee of $100.00 per child.

2.3.10    If both spouses are registered simultaneously, they will have equal rights. Therefore, both should be present during registration.

2.3.11    If spouses were registered as members in different years, their legal rights became applicable in the year they became members.

2.3.12    If the husband and wife divorce legally, the Edir will accept any legal document indicating which one should continue as a member of the Edir. A legal document includes an agreement between the husband and wife in a notarized letter. If there is unpaid payment, the person who continues as a member will inherit the balance.

2.3.13.   If a member and his spouse are divorced, both may continue paying the annual membership fee separately. However, they will lose the beneficiary if they decide not to continue paying the regular annual dues on time.

 

 

 

 

 

 

 

Article 2.4. Membership Fee.

2.4.1.     Membership                                                                      Registration                           Annual Fee

  • - Individual                                                                         $100.00                                  $360.00
  • - Member and his spouse                                                $200.00                                  $360.00
  • - Single parent (no limit to the number of children)    $200.00                                  $360.00
  • - Member and his spouse, including children,             $300.00                                  $360.00
  • - If a new member is added to the family
  •  (spouse and or children) _____________________ $100.00 per person

 

2.4.2.     Individual members or members with family will pay a thirty-dollar ($30.00) monthly fee calculated as one hundred and eighty dollars ($180.00) twice a year or a total of three hundred sixty dollars ($360.00) per year.

2.4.3      If many deaths occur among members due to a pandemic or unexpected accident and the total beneficiary payment is more than Edir's cash balance, the Board members or the general assembly will decide how much each beneficiary payment should be.

2.4.4.     If Edir's account balance is less than one hundred thousand dollars ($100,000), members will be requested to contribute more. In this instance, husband and wife, each one of them will contribute as a single member.

Article 3

3.1. Disciplinary Actions

3.1.1      The membership fee ($360.00) must be paid at the beginning of each New Year (January 1). A member will be considered in default, and an additional fee of one hundred dollars ($100) will be added if the annual payment is not paid within the year. The Edir will make a one-time warning phone call to a member to remind them to make the payment immediately.

3.1.2.     If a member skips the annual payment by over two (2) years, they will be removed from the membership, understanding that they canceled their membership deliberately.

 

 

 

 

 

 

 

Benefit Exercise Table 2

 

0-12 Months

1st yr. (12 months +)

2nd Yr. +

(a yr. +12 month)

3rd Yr. +

(2yr + 12 month)

4th Yr. + (in the 5th Yr.)

5th Yr. + (in the 6th Yr.)

 

Dinner

(if death occurs)

Dinner +

$10,000

Dinner +

$15,000

Dinner +

$20,000

Dinner +

$20,000

Dinner +

$20,000

Single/Married

2019

2020

2021

2022

2023

Scenario one

$460

$360

Passed away

 

 

Scenario two

$460

$360

$360

Member fee not paid

Passed Away

Scenario one.           A single or married person who has been a member since 2019 passed away in 2021. He had fully paid his membership fees for 2019 and 2020. Unfortunately, he passed away in 2021. He had not paid his 2021 membership fee. How much is the Beneficiary payment?

Note: the membership fee is due on January 1.

Answer:         $15,000 - $360 (membership fee for 2021, due on January 1) = $14, 640 and the file is closed. However, the file stays open for the married member under the spouse, and the 2021 payment is considered fully paid.

Scenario two.            A single person who has been a member since 2019 passed away in 2023. He had fully paid his membership fees for 2019, 2020 & 2021. Unfortunately, he passed away in 2023. He did not pay his 2022 and 2023 membership fees. How much is the Beneficiary payment?

Note:   The membership fee is due on January 1. He did not meet his 2022 obligation ($360 + $100 Penalty) and 2023 payment ($360). Therefore, the Payment is:

Answer:         $20,000 - ($360 + $100 + $360) = $19,180. The file will be closed for the single member, but the file of the married person will be transferred under the spouse's name, and the annual membership fees of 2022 and 2023 will be considered fully paid.

Note: Beneficiary benefit is calculated up to the year a full payment was made.

 

 

3.1.3      If a member is out of the USA for an undetermined time, prepayment of the annual fees is acceptable.

3.1.4.     A member removed from the membership for not paying his dues can be re-registered as a new member.

3.1.5.     If a member provides false evidence to the Edir and obtains undeserved (unnecessary, excessive) money or is found making an effort to do so, the Edir can remove them from the membership. The Edir can also take legal action to get back the obtained benefits.

3.1.6.     If a member is removed from the membership, the money they paid to the Edir will not be refunded.

3.1.7      The Edir has the right not to re-register the member who has been removed.

 

Article 4 The Leadership Team of the Edir

               The Edir has a General Assembly, the Board of Directors, Executives, and Auditors.

 

Article 4.1. The General Assembly

4.1.1.     The General Assembly is the general council in which all the members are included. It is the highest authoritative body of the Edir.

4.1.2.     The General Assembly is called for a meeting twice a year. The second meeting is for a picnic.

4.1.3.     The General Assembly, where more than half of the members are found in a meeting, is a full quorum.

4.1.4.     If the quorum is not achieved in the first meeting, the second meeting is considered a full quorum even if below half of the total members are in attendance.

4.1.5.     As stated in 4.1.3 and 4.1.4, the entire/whole assembly can pass any other decisions except the one indicated in Article 4.1.6.

4.1.6.     Two-thirds (2/3) of the total members' votes are required to dissolve the Edir.

4.1.7.     If the Edir dissolves, its movable and immovable assets, including cash, will be donated to the Ethiopian Community in Seattle.

 

Article 4.2. The Duty and the Authority of the General Assembly

4.2.1.     Elects the Board of Directors.

4.2.2.     Approves the Bylaws of the Edir.

4.2.3.     Approves the administrative budget of the Edir.

4.2.4.     Elects Auditors.

4.2.5.     Oversees how Edir's income is collected and recommends the expenditures of Edir's money.

4.2.6.     Hears the report of the Board, investigates, and gives instructions when needed.

 

Article 4.3. The Board of Directors

To administrate the Edir activities, the members will elect Board Members. The Board Members will directly report to the General Assembly. Their duties are as follows.

4.3.1      The number of Board members appointed is nine (9).

4.3.2.     The duration of the Board members' services is two (2) years. But, because of unforeseen/unexpected reasons, the board members' service can be extended for another two (2) continuous terms.

4.3.3.     The Board member who served in two (2) continuous terms must serve as a Board Consultant for at least one year before re-election. They will not have a voting right on the Board's decisions.

 

 

4.3.4.     When more than half of the Board members are present, it is a quorum.

4.3.5.     In any Board election, the members who served in the previous term will not be more than half or fifty percent (50%) of the new Board.

4.3.6.     If a Board member resigns from his duty before completing his term, the Board will assign a replacement member from within the Edir membership.

4.3.7.     During any Board election, if a member of the Executive Committee of the Board of Directors is re-elected for membership of the Board, they cannot maintain the same Executive Committee position held in the previous term.

 

Article 4.4 The Duties and Authorities of the Board of Directors

4.4.1.     The Board elects three (3) Executive Committee members from the Board members.

4.4.2.     Oversees and implements the decisions of the Board and the Executive Committee.

4.4.3      Presents the work performance report to the assembly within a pre-given period.

4.4.4.     Controls the total expenses of the Edir, which should not exceed the approved budget amount approved by the general assembly. The Board must justify the cost when the expenditure exceeds the approved amount by over ten percent (10%).

4.4.5.     None of the members of the Edir will be paid or compensated for the services they provide for the Edir.

4.4.6.     When necessary, the chairman of the Board may invite some senior citizens of Ethiopian origin or from other countries to be present in the meetings to share their experiences or advice. However, these consultants will not vote in the meetings apart from sharing their experiences and suggestions.

4.4.7.     The Board election will be conducted in the second year.

 

Article 4.5. Executive Committee and Duties

The Executive Committee includes a Chairperson, a Vice-Chairman, a Secretary, a Treasurer, a Public Relations Personnel, a Chief of Operations and Technology, and an Accountant.

4.5.1      The Board of the Edir will elect a Chairperson, Secretary, and Treasurer who conduct the daily operations of the Edir.

4.5.2.     Prepares a procedure manual for implementing the Board decisions.

4.5.3.     Establishes sub-committees as needed to perform the guidelines of the Board decisions.

4.5.4.     Performs its regular tasks, including chairing meetings.

4.5.5.     Presents a report to the Board of Directors.

4.5.6.     Collects the income of the Edir.

4.5.7.     Prepares forms for use.

4.5.8.     Ensures a member has received benefits according to the Bylaws.

4.5.9.     Oversees the dissemination of information to members.

4.5.10.   Insures the management of the property and monies of the Edir.

4.5.11. Researches how the Edir can be improved and implements any recommendation approved by the Board.

 

Article 4.6.The Chairperson

4.6.1      Chairs the Board meetings.

4.6.2      Plans the tasks of the Edir to be performed according to the Bylaws of the Edir.

4.6.3      Guides the work of the Edir, coordinates and supervises Executive Committee members.

4.6.4      Presents the performance reports of the meetings for the Board of Directors that are held periodically.

4.6.5      Calls the Board of Directors for meetings, including an emergency meeting, and gives suggestions/recommendations for when a general meeting will be held.

4.6.6      Approves and signs expenditures and letters on behalf of the Edir.

Article 4.7. The Deputy Chairperson

4.7.1.     Performs the Edir's tasks in the chairman's absence.

 

Article 4.8. The Secretary

4.8.1.     Keeps a list of the membership of the Edir.

4.8.2.     In consultation with the chairperson: - prepares the Executive Committee's plan and the General Assembly and will call the Executive Committee to meetings every month and members of the trustees every three months and then decide to call the entire members of the Edir.

4.8.3.     Takes the meeting minutes and delivers them to the Board.

4.8.4.     Conducts the secretariat office tasks of the Edir. Also, keeps original documents, copies of receipts, letters from government offices, permits, etc. No documents shall be burned, shredded, or trashed without the knowledge of the Board Members or the General Assembly.

Article 4.9. Treasurer

4.9.1.     Collects money and deposits it in the bank account of the Edir according to the Bylaws.

4.9.2.     Disburses funds due to the members upon the approval of the Board.

4.9.3.     Verifies that two executive committee members signed the checks.

4.9.4.     Prepares the budget of the Edir and implements it when approved.

4.9.5.     Ensures that the expenses are not over the approved budget.

Article 4.10. Accountant

4.10.1.   Manages the bookkeeping of the Edir.

4.10.2.   Oversees the receipts and the expenditures of the Edir.

4.10.3.   Verifies that Edir's income is collected appropriately.

4.10.4.   Maintains and reconciles bank books of the Edir.

4.10.5.   Prepares the accounting report of the Edir and presents it to the Board members.

4.10.6.   Prepares the tax documents that the government requires.

 

4.11. Public Relations

4.11.1.   Publicizes the tasks of the Edir.

4.11.2.   Establishes relationships with different institutions that have similar objectives.

4.11.3.   Prepares literature that will be publicized and promotes the Edir.

4.11.4.   Disseminate information about the organization, including Edir’s member situation. Makes sure that the pertinent data is delivered on time.

4.11.5.   Informs the Board of any assistance obtained from entities that may advance the objective of the Edir.

4.11.6.   Establishes relationships with organizations that may advance the objective of the Edir and presents a detailed report about their work to the Board of the Edir. Also, it paves the way for the Edir to serve the members better.

 

Article 4.12. Chief of the Operations and Technology

4.12.1.   Researches and reports how the operation of the Edir is facilitated.

4.12.2.   Provides necessary studies and performance reports to the Board about the institutions and services related to the Edir (such as the funeral homes, transport, and police).

4.12.3.   Provides a research report in which the Edir can benefit from insurance companies.

4.12.4.   Leads in forming a committee which is believed to be helpful to advance the Edir's activities in a new Technology.

4.12.5.   Helps the Edir to get legal status and maintain it.

4.12.6.   Guides establishing, administering, and developing the Edir's website.

4.12.7.   Gets the domain name for the website of the Edir, registers, and maintains it regularly.

4.12.8    Researches and recommends the optimal use of the website to the members.

 

Article 4.13. Auditors

4.13.1.   The Board of Directors appoints two members for the auditor's team in consultation with the general assembly.

4.13.2.   The auditors report to the Board of Directors.

4.13.3.   The auditors investigate the report prepared by financial experts and present it to the Board.

4.13.4.   The auditors may present monthly, quarterly, semiannual, or annual reports when the Board of Directors requests them as needed.

 

ARTICLE 5: BOARD OF TRUSTEES

 

Article 5.1 Structure and Responsibilities

 

5.1.1      A Board of Trustees consists of five (5) members.

 

5.1.2      The Vice President and the treasurer of the Board of Directors of Ethio Edir

               shall be members of the Board of Trustees by default. Ethio Edir Members

               shall elect three (3) individuals from the general members.

 

5.1.3      Among the three (3), one will be the trustee chairperson.

 

5.1.4      The Board of Trustees reports directly to the general assembly.

 

5.1.5      If one of the members cannot continue his duty for an unknown reason, the Ethio Edir Board members can nominate someone among the members. The Ethio Edir Board members must ensure that the Ethio Edir members know about the change.

 

5.1.6      The Board of Trustees shall consult with the Ethio Edir Board members about the security and safety of Ethio Edir's belongings and money.

 

5.1.7      If there is more than ten thousand dollars ($10,000.00) in expenditure, the Board of Trustees should be notified and approve the amount.

 

5.1.8      If the Board of Trustees disagrees with the activity of the Ethio Edir Board members, the Trustees can bring the matter to the Ethio Edir Board meeting. Then, if the issue is not resolved, the Trustees can call a general assembly meeting.

 

5.1.9      The Board of Trustees can accept grievances from the members.

 

5.1.10    The Board of Trustees will review the Bank Statements (if possible, every month, if not every three months).

   

5.2 Election and term of office of Board of Trustees

 

5.2.1      The three (3) Board of Trustees candidates elected from among members shall serve for three years.

 

5.2.2      If a Board of Trustees member resigns, the Ethio Edir Board can nominate new members to serve until the next general assembly.

 

5.2.3      The General Assembly may extend its term for another three (3) years if it finds this to be in the best interests of the Edir.

 

Chapter 6 The Bylaw of the Edir

6.1.         This Bylaw can be called the Bylaw of Ethio Edir as amended in 2022 and implemented as of January 1, 2022.

6.1.1.     Ethio Edir's task and accounting commence on January 1 and close on December 31 each year. The annual Cycle is from January 1 to December 31.

  


Ethio Edir is a 501(c)(12) non-profit organization. 

P.O. Box 22752 | Seattle, WA 98122; Email: contact@ethioedir.org | Tel. (206) 395 -8014

Powered by Wild Apricot Membership Software