ኢትዮ እድር የአባላት መረጃ አያያዙንና የክፍያ ስርአቱን የተሻለ ለማድረግ በማሰብ አዲስ ዘመናዊ አሠራር በሥራ ላይ እያዋለ ይገኛል። ይህ ዋይልድ አፕሪኮት በተሰኘ ሲስተም ላይ የተደራጀ የኦንላይን የክፍያ መንገድ ለአባላት ተጨማሪ የክፍያ አማራጭ ይሰጣል ተብሎ ይታመናል። ከዚህ በኋላ አባላት ከቼክና ካሽ በተጨማሪ በደቢትና ክሬዲት ካርዶች ክፍያቸውን ማከናወን ይችላሉ። ከዚህም በተጨማሪ፣ አዲሱ የክፍያ ዘዴ ከአባላትና ሌሎች ወገኖች ሊገኝ የሚችለውን እርዳታ በቀላሉ ለማሰባሰብ ይረዳል።
አባላት አዲሱን ሲስተም በተቻለ መጠን እንዲለማመዱትና በስፋት እንዲጠቀሙበት የኢትዮ እድር ቦርድ በዚህ አጋጣሚ ጥሪውን ያቀርባል።